SHASHE MEDIUM CLINIC

Call us for any question

0468103905 / 0993788686

Shashemenne Jamaican Sefer, Behind NOC Gas Station

Ethiopia

Office Hour: 08:00am - 05:30pm

info@shasheclinic.com

የሚጥል በሽታ ያለባቸዉ ሰዎች ላይ ማንቀጥቀጥ እንዲቀሰቀስ የሚያደርጉ ነገሮች

18,August 2121

የሚጥል በሽታ ያለባቸዉ ሰዎች ላይ ማንቀጥቀጥ እንዲቀሰቀስ የሚያደርጉ ነገሮች

የሚጥል ህመም ያላቸዉ ሰዎች ላይ ህመሙ እንዲቀሰቀስ የሚያደርጉ ነግሮች አሉ። እነዚህ ነገሮች በተለምዶ ቀስቃሽ ይባላሉ። ቀስቃሾች የሚጥል በሽታ እንዲመጣ  የሚያደርጉ ወይም የሚያስከትሉ ሳይሆኑ መንቀጥቀጥ ወይም መራድ እንዲቀሰቀስ ያደርጋሉ። የሚጥል በሽታ ያለባቸው ሰዎች ሁሉ የመራድ ወይም ማንቀጥቀጥ ቀስቃሽ ምልክቶች ይኖራቸዋል ማለት አይደለም። እንዲሁም አንድን ሰው ላይ መራድን ወይም ማንቀትቀጥን  የሚቀሰቅሱ ነገሮች በተመሳሳይ የሚጥል በሽታ ያለባቸው ሌሎች ሰዎችን ላይ እንዲከሰት ላያደርጉ  ይችላሉ። የሚጥል ህመም ያለባቸዉን ሰዎችን ማንቀጥቀጥ እንዲከሰት ከሚያደርጉ ነገሮች ዉስጥ

·         የታዘዘልዎን የሚጥል በሽታ መድሃኒቶች በታዘዘዉ መሰረት አለመዉሰድ፦ የሚጥል በሽታ መድኃኒቶችን ሀኪም ባዘዘልዎ መሰረት በመደበኛነት መውሰድ መድኃኒቱ በደምዎ ውስጥ ሳይቀንስ በትክክለኛ ደረጃ ለማቆየት ይረዳል። ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከታዘዘልዎ መድሃኒት ዉስጥ አንድ ቀን እንኳ መድሃኒትዎን አለመዉሰድ የሚጥል በሽታ ምልክት የሆነዉ ማንቀጥቀጥ እንዲከሰት ያደርጋል።

·         የድካም ስሜት እና ጥሩ እንቅልፍ አለመተኛት፦ የሚጥል በሽታ ያለባቸው ብዙ ሰዎች የድካም ስሜት ወይም ጥሩ እንቅልፍ ማጣት ማንቀጥቀጥ እንዲከሰት ያደርጋል።

·         ጭንቀት፦ በውጥረት ወይም ጭንቀት ምክንያት  የመራድ ወይም ማንቀጥቀጥ ችግር  ለምን እንደሚነሳ በትክክል አይታወቅም። ነገር ግን የሚጥል በሽታ ያለባቸው ብዙ ሰዎች ውጥረት ከተሰማቸው ማንቀጥቀጥ የመቀስቀስ ዕድሉ ከፍተኛ ነው።

·         አልኮልና አደንዛዥ መድሃኒቶች፦የሚጥል በሽታ ያለባቸዉ ሰዎች አልኮል የሚጠጡ ከሆነ ለማንቀጥቀጥ መከሰት ምክንያት ሊሆን ይችላል። ከከባድ መጠጥ በኋላ ፣ አልኮሆል ከሰውነትዎ እየወጣ ሲመጣ ማንቀጥቀት የመከሰት ዕድል ከፍተኛ ነው። ይህ የማንቀጥቀጥ ተጋላጭነት ብዙውን ጊዜ  የሚከሰተዉ ከጠጡ በኋላ ከ 6 እስከ 48 ሰዓታት መካከል ነው።

·         ብልጭታ ወይም ብልጭ ድርግም የሚሉ መብራቶች፦ የሚጥል በሽታ ካለባቸው ከ 100 ሰዎች ውስጥ 3 ገደማ የሚሆኑት ብልጭ ድርግም በሚሉ ወይም በሚያንጸባርቁ መብራቶች ወይም የነሱ ተመሳሳይ ድግግሞሽ የተነሳ መጣል ወይም ማንቀትቀጥ ሊያስነሳባቸዉ ይችላል። ይህ ፎቶሴንሴቲቭ ኢፒለብሲ ይባላል። ፎቶሴንሴቲቭ የሚጥል በሽታ ከለብዎ ማንቀጥቀጡ በተፈጥሮ ወይም ሰዉሰራሽ መብራቶች ሊቀሰቀስ ይችላል።

·         ምግብ በስርዓቱ አለመመገብ፦ የመመገቢያ ሰዓትዎን በትክክል አለመጠበቅና የምግብ ጊዜን መዝለል ለማንቀጥቀጥ መቀስቀስ ምክንያት ሊሆን ይችላል። በተጨማሪም በቁ ፈሽእስ አለመጠጣት፣ የመዕድናትና የቫይታሚን እጥረቶች ተመሳሳይ ችግር እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል።

·         ትኩሳት የሚያመጡ ህመሞች መከሰት፦ የሰዉነት ሙቀትን ሊጨምሩ ይሚችሉ ህማሞች ወይም እንፌክሽኖች መከሰት ማንቀትቀት እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል።

·         የወር አባ ዑዳት ወይም ሌሎች ሆርሞን መዛባቶች፦ በወር ኣበባ ዑዳት ወቅት የሆርሞን መለዋወጥ ስለሚኖር ለማንቀጥቀጥ መቀስቀስ ምክንያት ሊጅሆን ይችላል


You May Also Like

24 Hour Emergency

Open round the clock for conve-nience, quick and easy access

Complate Lab Services

Cost-efficient, comprehensive and clinical laboratory services

Medical Professionals

Qualified and certified physicians for qulity medical care

EMERGENCY CALL: