SHASHE MEDIUM CLINIC

Call us for any question

0468103905 / 0993788686

Shashemenne Jamaican Sefer, Behind NOC Gas Station

Ethiopia

Office Hour: 08:00am - 05:30pm

info@shasheclinic.com

የሚጥል በሽታ እንዴት ይከሰታል

11,August 2121

የሚጥል በሽታ እንዴት ይከሰታል

ክፍል ሁለት

የሚጥል ህመም ተላላፊ በሸታ አይደለም። ምንም እንኳን  ለሚጥል በሽታ ብዙ ህመሞች እንደ መሠረታዊ መነሻ ቢሆኑም ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ እስከ 50  በመቶ የሚሆኑ ታማሚዎች  የሚጥል በሽታዉ  መንስኤ እስካሁን አይታወቅም። የሚጥል በሽታ መንስኤዎች በሚከተሉት ምድቦች ሊከፈል ይችላል እነርሱም የአንጎል መዋቅራዊ ችግር፣ በዘር የሚመጣ ፣ በኢንፌክሽን ምክንያት ፣ ሜታቦሊና ምክንያቱ የማይታወቅ ናቸዉ። መንስኤዎቹ  የሚከተሉትን ያካትታሉ:

·         በቅድመ ወሊድ ወይም በወሊድ ምክንያት የአንጎል ጉዳት ( የኦክሲጂን እጥረት፣ በወሊድ ውቀት በሚደርስ ጉዳት እንዲሁም ሲወለዱ ከክብደት በታች መሆን)

·         ከተዛማጅ የአንጎል ችግር ጋር የተወለዱ የአፈጣጠር ችግር አሊያመ በዘር የሚመጡ ችግሮች

·         ከባድ የችንቅላት ጉዳት

·          ወደ አንጎል የሚሄድ ኦክስጅን መጠንን የሚገድብ ስትሮክ መከሰት

·         የአንጎል ኢንፌክሽኖች፦ የማጅራት ገትር፣ ኢንሴፍላይትስና ኒዮሮሲስቲሰርኮሲስ

·         የአንጎል ዕጢ

·         በዘር የሚተላልፉ ችግሮችና የመሳሰሉት ናቸዉ።

የሚያመጣቸዉ ጉዳቶች

• መዉደቅ፦ ህመሙ በሚጥሎት ወቅት የማይሆን ቦታ ከወደቁ ፣ የጭንቅላት ጉዳት ወይም የአጥንት መሰበር ሊከሰት ይችላል።

• መስመጥ፦እየዋኑ ወይም ሻወር ሲወስዱ ከጣለዎ በድንገት የመስጠም አደጋ ሊገጥምዎ ይችላል።

• የመኪና አደጋ፦ መኪና እየነዱ ወይም ማሽን ላይ እየሠሩ ከሆነ የሚጥል ህመም ካጋጠመዎ  አደገኛ ሊሆን ይችላል።

• ነፍሰጡር ከሆኑ፦ ነፍሰጡር ሆነዉ የሚጥል ህመም ወይም ማንቀጥቀጥ ካጋጠመዎ ለእርስዎም ይሁን ለፅንሱ አደገኛ ነዉ። እንዲሁም የተወሰኑ ለሚጥል ህመሙ የሚሰጡ መድሃኒቶች በፅንሱ ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ስለሚችሉ መድሃኒት እየወሰዱ ከሆነና ነፍሰጡር ከሆኑ አሊያም ለማርግዝ ዕቅድ ካለዎ የህክምና ባልሙያዎን ያማክሩ።

• የስሜት መጎዳት፦ የሚጥል በሽታ ያላቸዉ ሰዎች ብዙውን ጊዜ እንደ ድብርትና ጭንቀት ያሉ የስነልቦና ችግሮች ይኖራቸዋል። ይህም ችግሮቹ ከራሱ ሁኔታ ጋር የተያያዙ አሊያም የመድኃኒት የጎንዮሽ ጉዳቶች ውጤት ሊሆኑ ይችላሉ።

ህክምና

እስከ 70% የሚሆኑ የሚጥል በሽታ ያለባቸው ሰዎች ተገቢዉን ህክምና ማለትም ለሚጥል ህመም የሚሰጠዉን በትከከል እየወሰዱ የሚከታተሉ ከሆነ ከሚጥለዉ  ወይም ከማንቀጥቀጥ ነፃ ሊሆኑ ይችላሉ።

የሚጥል በሽታ ያላባቸዉ ሰዎች ተገቢዉን ህክም መዉሰድና ክትትል ማድረግ ይጠበቅባቸዋ።

 

መከላከል

በግምት እስከ 25 በመቶ የሚሆኑ  የሚጥል በሽታዎችን  መከላከል ይቻላል።  ለመከላከል ከሚረዱ መንገዶች

·         የጭንቅላት ጉዳት እንዳይደርስ መከላከል  ከአደጋ በኋላ ከሚከሰት የሚጥል በሽታ ለመከላከል በጣም ውጤታማው ዘዴ ነው።

·         በቂ የቅድመ ወሊድ እንክብካቤ ማድረግ፦  ይህ በወሊድ ጉዳት ምክንያት የሚከሰተውን በሚጥል በሽታ የመያዝ እድልን ይቀንሳል።

·         ህፃናት ትኩሳት ሲኖራችዉ የሰውነት ሙቀት መጠን መቀነስ፦ መድሃኒቶችንና ሌሎች ዘዴዎችን በመጠቀም ትኩሳታቸዉን መቀነስ በትኩሳት ምክንያት የሚመጣን መጣል ወይም መንቀጥቀጥ (ferile seizure)  የመያዝ እድልን ሊቀንስ ይችላል።

·         ከስትሮክ ጋር ተያይዞ የሚመጣን የሚጥል በሸታ ለመከላከል ለልብና ለደም ቧንቧ ችግር ሊያጋልጡ የሚችሉ ችግሮችን መቀነስ

·         የጭንቅላት ( አዕምሮ) ኢንፌክሽኖችን መከላከል፦ ከሰሃራ በረሃ በታች የሚጥል በሽታ በብዛት እንዲከሰት ከሚያደርጉ ነገሮች ዉስጥ የአንጎል ኢንፌክሽኖች ዋናዎቹ ናችዉ።  


You May Also Like

24 Hour Emergency

Open round the clock for conve-nience, quick and easy access

Complate Lab Services

Cost-efficient, comprehensive and clinical laboratory services

Medical Professionals

Qualified and certified physicians for qulity medical care

EMERGENCY CALL: