SHASHE MEDIUM CLINIC

Call us for any question

0468103905 / 0993788686

Shashemenne Jamaican Sefer, Behind NOC Gas Station

Ethiopia

Office Hour: 08:00am - 05:30pm

info@shasheclinic.com

ለስኳር ህመም ሊያጋልጡ የሚችሉ ነገሮች

16,August 2121

ለስኳር ህመም ሊያጋልጡ የሚችሉ ነገሮች

የስኳር ህመም የተለያዩ አይነቶች አሉት። ይህም አይነት አንድ፣ አይነት ሁለት፣ በእርግዝና ወቅት የሚከሰትና በሌሎች ህመሞች ምክንያት የሚከሰት ተብሎ ይከፈላል። ለስኳር በሽታ የሚያጋልጡ ምክንያቶች እንደስኳር በሽታዉ ዓይነት ይወሰናል።

ለአይነት አንድ (Type I diabetes) የስኳር አይነት የሚያጋልጡ ነገሮች

አይነት አንድ የስኳር አይነት የራሳችን የበሽታ መከላከል የራሳችንን ሴሎች በሚያጠቃበት ወቅት የሚከሰት ነዉ ተብሎ ይታሰባል። ለህመም ሊያጋልጡን ከሚችሉ ነገሮች ዉስጥ

·         በቤተሰብ ዉስጥ መሰል ችግር መኖር፦ በቤተሰብ ዉስጥ ማለትም አናትና አባት፣እህት ወንድም አይነት አንድ ስኳር መኖር

·         እድሜ፡- አይነት አንድ ስኳር በየትኛዉም የዕድሜ ደረጃ የሚከሰት ቢሆንም በብዛት ሊከሰት የሚችለዉ ግን በልጅነት፣በታዳጊዎችና ወጣቶች ላይ ነዉ።

  • ከባቢያዊ ሁኔታዎች፦ ለአንዳንድ የቫይረስ ህመሞች መጋለጥ አይነት አንድ የስኳር ህመም እንዲከሰት ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ
  • የራሳችንን ሴሎች ሊጎዱ የሚችሉ የበሽታ ተከላከይ ሴሎች ( አዉቶአንቲቦዲዎች) መኖር፦

ለአይነት ሁለት (Type II diabetes) የስኳር አይነት ሊያጋልጡ የሚችሉ ነገሮች

·         ቅድመ-ስኳር (prediabetes) መኖር

·         ያሰዉነት ክብደትዎ ከፍተኛ ከሆነ

·         ዕድሜዎ ከ45 ዓመትና ከዚያ በላይ መሆን

·         በቤተሰብ ዉስጥ ማለትም አናትና አባት፣እህት ወንድም አይነት ሁለት ስኳር መኖር

·         ፖሊሲስቲክ ኦቫሪያን ሲንድረም የሚባል የሆርሞን መዛባት ችግር መኖር

·         በሳምንት ከ 3 ጊዜ በታች አካላዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ

·         በእርግዝና ወቅት የስኳር ህመም ተከስቶ ከነበረ ወይም ከ4 ኪሎ በላይ የሚመዝን ህፃን ወልደው የሚያውቁ

·         ከመጠጥ ጋር ያልታያያዘ የጉበት ስብ መሆን ችግር ካለዎ

·         ከፍተኛ የሆነ የሰዉነት ስብ መጠን( የኮሌስትሮልና ትራይግለሴራይድ መጠን) መኖር

ከእርግዝና ጋር የተያያዘ የስኳር ህመም (Gestational diabetes)

·         ቀደም ባሉት የእርግዝናዎ ወቅቶች ከእርግዝና ጋር የተያያዘ ስኳር መኖር

·         ከዚህ ቀደም 4 ኪሎና ከዚያ በላይ የሆነ ልጅ ወልደዉ ከሆነ

·         የሰዉነትዎ ክብደት ከመጠን በላይ ከሆነ

·         ዕድሜ ከ25 ዓመት በላይ መሆን

·         በቤተሰብ ዉስጥ አይነት ሁለት ስኳር ህመም መኖር

·         ፖሊሲስቲክ ኦቫሪያን ሲንድረም የሚባል የሆርሞን መዛባት ችግር መኖር


You May Also Like

24 Hour Emergency

Open round the clock for conve-nience, quick and easy access

Complate Lab Services

Cost-efficient, comprehensive and clinical laboratory services

Medical Professionals

Qualified and certified physicians for qulity medical care

EMERGENCY CALL: