SHASHE MEDIUM CLINIC

Call us for any question

0468103905 / 0993788686

Shashemenne Jamaican Sefer, Behind NOC Gas Station

Ethiopia

Office Hour: 08:00am - 05:30pm

info@shasheclinic.com

የሚጥል በሽታ

11,August 2121

የሚጥል በሽታ

ክፍል አንድ

የሚጥል በሽታ ታላላፊ ያልሆነ፣ ስር የሰደደና በየትኛዉም ዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎች ላይ ሊከሰት የሚችል የአዕምሮ (የአንጎል) ህመም ነዉ። የህመሙ መገለጫ ከሆኑት ዉስጥ በተድጋጋሚ የሚመጣ ማንቀጠቀጥ ሲሆን ይህም ለአጭር ጊዜ የሚቆይና  ከእርስዎ ቁጥጥር ዉጪ በሆነ መልኩ የተወሰኑ የካል ክፍልን (በከፊል) ወይም መላውን አካል (በአጠቃላይ) ሊያካትት የሚችልና በተጨማሪም አንዳንድ ጊዜ እራስን መሳትና የአንጀት ወይም የፊኛ ተግባርን መቆጣጠር አለመቻል እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል።

እንደ የአለም ጤና ድርጅት መረጃ በዓለማችን 50 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የሚጥል በሽታ ያላቸዉ ሲሆን ይህም የሚጥል በሽታን በዓለም አቀፍ ደረጃ በጣም ከተለመዱት የነርቭ በሽታዎች አንዱ እንዲሆን አድርጎታል። ከዚህ ዉስጥ 80 በመቶ ያሚሆኑት ታማሚዎቸ የሚገኙት ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸዉ ሀገሮች ነዉ። የሚጥል በሽታ ካለባቸው ሰዎች መካከል 70% የሚሆኑት በትክክል ከተመረመሩና አስፈላጊዉን ህክምና ከተደረገላቸው ከማንቀጥቀጥ ነጻ ሆነው እንደሚኖሩ ይገመታል።

የሚጥል ህመም የሚከሰተዉ የተወሰኑ የአንጎል ሴሎች ከመጠን ያለፈ የኤሌክትሪክ ፍሰት በሚኖራችዉ ወይም በሚለቁበት ወቅት ነዉ። ይህ ከተለያዩ የአንጎል ክፍሎች ሊነሳ ይችላል። አንድ ሰዉ አንድ ጊዜ ብቻ ማንቀጥቀጥ ቢያጋጥመዉ የሚጥል በሽታ አለዉ ማለት አይደለም። አንድ ሰዉ የሚጥል በሽታ አለዉ የሚባለዉ ምክንያት የሌለዉ ወይም ያልታሰበ የሚያንቀጠቅጥ ህመም ወይም መራድ ለሁለት ጊዜና ከዚያ በላይ ሲያጋጥመዉ ነዉ።

የሚጥል በሽታ ፎካልና ጄኔራላይዝድ በመባል በ2 ይከፈላል።

 የህመም ምልክቶች

የህመም ምልክቶቹ እንደሚጥል በሽታዉ አይነት ከቀላል እስከ ከባድ ደረጃ ሊሆኑ ይችላሉ። ምልክቶቹም

• ጊዜያዊ የሆነ ግራ መጋባት

• ለተወሰን ጊዜ ራስን መሳትና ግንዛቤ ማጣት

• አንድ ቦታ ላይ አይንን ተክሎ ፈዞ መቅረት

• የእንቅስቃሴ ፣ የስሜት ህዋሳት(እይታ ፣ መስማትና ጣዕም) እንዲሁም የባህሪና ሌሎች የእውቀት (ኮግኒቲቭ) ተግባራት መዛባት

• ከታማሚዉ ቁጥጥር ዉጪ የሆነ የእግርና የእጅ መወራጨት (Uncontrollable jerking movements)

• እንደ ፍርሃትና ጭንቀት ያሉ  የእውቀት (ኮግኒቲቭ) ወይም ስሜታዊ ምልክቶች መታየት


You May Also Like

24 Hour Emergency

Open round the clock for conve-nience, quick and easy access

Complate Lab Services

Cost-efficient, comprehensive and clinical laboratory services

Medical Professionals

Qualified and certified physicians for qulity medical care

EMERGENCY CALL: