SHASHE MEDIUM CLINIC

Call us for any question

0468103905 / 0993788686

Shashemenne Jamaican Sefer, Behind NOC Gas Station

Ethiopia

Office Hour: 08:00am - 05:30pm

info@shasheclinic.com

የሆድ ድርቀት ምልክቶች

09,August 2121

የሆድ ድርቀት ምልክቶች

በሳምንት ከ3 ጊዜና ከዚያ በታች ለሆነ ጊዜ ሰገራ መዉጣት
ሰገራዎ ደረቅና ጠንካራ መሆን
ሲፀዳዱ ህመም መኖርና ለማዉጣት መቸገር
የሆድ ህመም ወይም ቁርጠት መኖር
የሆድ መነፋትና የማቅለሽለሽ ስሜት መኖር
መፀዳጃ ቤት ሄደዉ ከተፀዳዱ በኃላ አንጀትዎን ሙሉ በሙሉ ባዶ እንዳላደረጉ የሚሰማዎት ስሜት መኖር ናቸዉ።
ሊደረግ የሚችሉ ህክምና
አብዛኛዎቹ መለስተኛ እና መካከለኛ የሆድ ድርቀት ችግሮች በቤትዎ እራስዎ በመዉሰድ በቤትዎ ዉስጥ ሊያክሙት ይችላሉ። ድርቀትን ሊቀንሱ የሚችሉ
በቀን ተጨማሪ ከ2 እስከ 4 ብርጭቆ ዉሃ መጠጣት። የፈሳሽ ምጣኔን ሊቀንሱ የሚችሉ ካፊን ያለባቸዉን ፈሳሾችና መጠጥ ከመጠጣት መቆጠብ
ፍራፍሬ ፣ አትክልትና ጥራጥሬን ጨምሮ ከፍተኛ ፋይበር ያላቸዉ ምግቦችን መመገብ፤ እንደ ስጋ፣እንቁላልና አይብ ያሉ የስብ ይዘታቸዉ ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን መቀነስ
ለድርቀት ሊዳርጎት የሚቺሉ ምግቦችን መለየት
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድራግ
መጸዳጃ ቤት ለመፀዳዳት ሲቀመጡ እንዴት እንደሚቀመጡ ያስተዉሉ። እግርዎን ከፍ በማድረግ፣ትንሽ ወደኃላ ደገፍ በማለት ወይም ቁጢጥ ማለት በቀላሉ ለመፀዳዳት/ሰገራን ለማዉጣት ይረዳዎታል።
አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የሰገራ ማለስለሻ መድሃኒት መዉሰድ። ሀኪምዎን ሳያማክሩ የሰገራ ማለስለሻ ከሁለት ሳምንታት በላይ እንዳይወስዱ። መለስለሻን ከልክ በላይ መዉሰድ የህመም ምልክቶቹን ሊያባብሳችዉ ይችላል። ለመፀዳዳት ሲቀመጡ ከማንበብ፣ ስልክዎን ጨምሮ ሌሎች መሳሪያዎችን ከመጠቀም ይቆጠቡ።
ድርቀትን መከላከል
ድርቀት ስር የሰደደ ችግር እንዳይሆን ለመከላከል በቤት ዉስጥ ሲጠቀሙባቸዉ የነበሩ ዘዴዎችን መጠቀም ያስፈልጋል።
የተመጣጠነና የፋይበር ይዘታቸዉ ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን መጠቀም፦ የፋይበር ይዘታችዉ ከፍተኛ የሆኑ ምግቦች የሚባሉት አትክልት ፣ፍራፍሬ፣ የአበባ እህሎች፣ ጥራጥሬዎችና አዝርዕቶች ናቸዉ።
በቀን ቢያንስ 8 ብርጭቆና ከዚያ በላይ ዉሃ መጠጣት፦ እንደ ቡናና ኮካ ያሉ ካፊን ያላቸዉ ፈሳሾች ሰዉነትን ብዙ ፈሳሽ ስለሚያሳጡ ድርቀትን ያባብሳሉ።ስለሆነም ድርቀት ካለዎ እነዚህን ፈሳሾች ከመጠጣት ይቆጠቡ። በአንዳንድ ሰዎች ላይ ወተት ድርቀትን ሊያባብስ ይችላል።
በመደበኛነት ያአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
ሰገራ የመምጣት ስሜት ሲኖርዎ ወደ መፀዳጃ ቤት ይሂዱ፤ ስሜቱ እያለዎ መቆየት ድርቀት እንዲባባስ ያደርጋል።ስለሆነም ስሜት እያልዎ መቆየት አይመከርም።
አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
9424
+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.

You May Also Like

24 Hour Emergency

Open round the clock for conve-nience, quick and easy access

Complate Lab Services

Cost-efficient, comprehensive and clinical laboratory services

Medical Professionals

Qualified and certified physicians for qulity medical care

EMERGENCY CALL: