SHASHE MEDIUM CLINIC

Call us for any question

0468103905 / 0993788686

Shashemenne Jamaican Sefer, Behind NOC Gas Station

Ethiopia

Office Hour: 08:00am - 05:30pm

info@shasheclinic.com

የሆድ ድርቀት( constipation)

04,August 2121

የሆድ ድርቀት( constipation)

አንድ ሰዉ ድርቀት አለዉ የሚባለዉ በሳምንት ዉስጥ ከሶስት ጊዜና ከዚያ በታች ሰገራ የሚቀመጥ ከሆነ ነዉ። ሰገራ ሳይቀመጡ በቆዩ ቁጥር ሰገራዉ እየደረቀ ስልሚመጣ ይበልጥ ለማዉጣት ይቸገራሉ። ድርቀት ካልዎ

·         ሰገራዉ ደረቅና ጠንካራ ይሆናል

·         ለመፀዳዳት መፀዳጃ ቤት ሲሄዱ ሰገራዉን ለማዉጣት ህመም ስለሚኖርዎ ለማዉጣት ይቸገራሉ

·         መፀዳጃ ቤት ሄደዉ ከተፀዳዱ በኃላ አንጀትዎን ሙሉ በሙሉ ባዶ እንዳላደረጉ የሚሰማዎት ስሜት ይኖሮታል።

የአንጀት ድርቀት በዓለማችን በብዛት ከሚከሰቱ የአንጀት ችግሮች ዉስጥ አንዱ ነዉ። በሁሉም ዕድሜ ያሉ ሰዎች አልፎ አልፎ የሆድ ድርቀት ሊኖራቸው ይችላል።

አንዳንድ ሰዎችና የተወሰኑ የጤና ሁቴታዎች ለበተከታታይ የሆድ ድርቀት (ሥር የሰደደ የሆድ ድርቀት) የመከሰት እድል እንዲኖር  ያደርጋል። እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ:

·         እርጅና ( በእድሜ መግፋት)፦ በእድሜ የገፉ ሰዎች እንቅስቃሴ የማድረግ እድላቸዉ ይቀንሳል፣ በዚህም የተነሳ ወጣት ከነበሩበት አንፃር የአንጀት ጡንቻዎች የመኮማተር ጥንካሬ ይቀንሳል ፣የምግብ የመፈጨት ሂደት( ሜታቦሊዝማቸዉ) ዘገምተኛ ይሆናል

·         ሴት መሆን( በተለይ ነፍሰጡር ስትሆን እና ከወሊድ በኋላ)፦በእርግዝናና ጡት ማጥባት ወቅት የሆርሞን መለዋወጥ ስለሚኖር ለድርቀት መከሰት ምክንያት ይሆናል።

·         በቂ ፋይበር ያለዉ ምግብ ያለመመገብ፦ ከፍተኛ ፋይበር ያላቸው ምግቦች ምግብ በምግብ መፍጫ ሥርዓት ውስጥ በደንብ እንዲንቀሳቀስ ያደርጋሉ።  

·         የተወሰኑ መድሃኒቶች

·         የተወሰኑ የነርቭ ችግሮች፦የህብለ ሰረሰርና የአንጎል ችግሮች ለድርቀት መከሰት ምክንያት ይሆናሉ።      

የሆድ ድርቀት ምክንያቶች

ብዙ የሆድ ድርቀት ምክንያቶች አሉ። የአኗኗር ዘይቤ ምርጫዎች ፣ መድኃኒቶች ፣ የሕክምና ሁኔታዎች እና እርግዝና ዋና ዋናዎቹ ናችዉ።

ድርቀትን እንዲከሰት የሚያደርጉ ነገሮች

·         የፋይበር ይዘታቸዉ አነስተኛ የሆኑ ምግቦችን መመገብ( ማዘዉተር)

·         በቂ ፈሳሸ ውይም ዉሃ ያለመጠጣት

·         በቂ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድራግ

·         ጭንቀት

·         የሰግራ ስሜት ሲኖርዎ መፀዳጃ ከመሄድ መቆጠብ

·         መድሃኒቶች

·         የዉስጥ ደዌ ችግሮች፦ የሆርሞን መዛባት፣ የአንጀት ችግሮች( ካንሰር፣ ኢሪተብል በወል ሲንድሮም፣የነርቭ ችግሮችና የመሳሰሉት) ናቸዉ።


You May Also Like

24 Hour Emergency

Open round the clock for conve-nience, quick and easy access

Complate Lab Services

Cost-efficient, comprehensive and clinical laboratory services

Medical Professionals

Qualified and certified physicians for qulity medical care

EMERGENCY CALL: