SHASHE MEDIUM CLINIC

Call us for any question

0468103905 / 0993788686

Shashemenne Jamaican Sefer, Behind NOC Gas Station

Ethiopia

Office Hour: 08:00am - 05:30pm

info@shasheclinic.com

በካርቦን ሞኖኦክሳይድ መመረዝን መከላከል

31,July 2121

በካርቦን ሞኖኦክሳይድ መመረዝን መከላከል

ክፍል ሁለት

·         በመኖሪያ ቤት ዉስጥ ከሰልን ጨምሮ ሌሎች ካርቦንሞኖኦክሳይድ የሚያውጡ ነገሮችን ቢቻል አለመጠቀም። የምንጠቀም ከሆነ ደግሞ ከተጠቀምን በኃላ በአግባቡ በጥፋቱን ማረጋገጥ፣ ክፍሉ በቂ አየር እንዲዘዋወርባት በርና መስኮትን መክፈት

·         በርና መስኮቶች ክፍት ቢሆኑም እንኳ ጄኔሬተርን ፣ በግፊት የሚያጥብ ማሽን  ወይም በቤንዚን የሚያንቀሳቅስ ሞተር በቤት ቤዝመንት ፣ ጋራዥ ወይም ሌላ በተዘጋ ቦታ ውስጥ  እንዲሰሩ በጭራሽ አለማድረግ ፡፡

·         የሞተር ተሽከርካሪን ፣ ጄነሬተር ፣ የግፊት ማጠቢያ ወይም ማንኛውንም ቤንዚን የሚያንቀሳቀሱ ሞተሮች አስነስተዉ እንዲሰራ ሲያደርጉ ክፍት ከሆንዉ ቤትዎ በር ወይም መስኮት ከ6ሜትር ባነሰ ርቀት አይሁን ወይም  አየር እንደልብ በማይዘዋወርበት ዝግ ቦታ መሆን የለበትም።

·         የመኪናዎን ሞተር ይሁን ሌሎች ሞተሮች በተዘጋ ወይም በከፊል በተዘጋ ክፍል ወይም ጋራዥ ዉስጥ አስነስተሁ እንዲሰራ አለማድረግ።

·         ቆሻሻ የአየርና ይጭስ መተላልፊያ ቀዳዳዎችን ሊዘጋ ስለሚችል የአየርና የጭስ መተላለፊያ  ቀዳዳዎችን ክፍት መሆናችዉን ያረጋግጡ

·         የአየር ማሞቂያ ስርዓቶች፣ የዉሃ ማሞቂያዎች፣ በከሰልና ጋዝ የሚሰሩ ዕቃዎች አመታዊ ጥገና በባልሙያዎች እንዲደረግ ማድረግ።

·         የካርቦን ሞኖኦክሳይድ መጠቆሚያ (CO detector) በቤትዎ ዉስጥ ካለዎ በየጊዜዉ ባትሪዉን መቀየርዎን አለመርሳት

·         በነዳጅ የሚንቀሳቀሱ መሳሪያዎች ያሉበት ክፍል በትከከል የአየር ዝዉዉር እንዲኖረዉ ማድረግ

ለካርቦንሞኖኦክሳይድ የተጋልጠ ሰው ምን ማድረግ አለበት

·         ከክፍሉ በፍጥነት ወጥቶ ንፁህ አየር ማግኘት፦ ጭስ ያለበት ክፍል ከቆዩ ራስን መሳትና ለህልፈተ ህይወት ሊዳርጉ ይችላሉ።

·         ወድ ህክምና ባለሙያዎ በፍጥነት በመሄድ የህክመና ምክርና ዕርዳታ ማግኘት፦ በተለይ በካርቦንሞኖ ኦክሳይድ የመመረዝ የህመም ምልክቶቹ ካለዎ የህክምና ባልሙያዎን ያማክሩ

 

በካርቦን ሞኖኦክሳይድ መመረዝ የሚያመጣቸዉ የጎንዮሽ ጉዳቶች

እንደ ተጋለጡበት መጠንና እርዝማኔ በካርቦን ሞኖኦክሳይድ መመረዝ የሚከተሉትን የጎንዮሸጉዳቶች

·         ዘላቂ የአንጎል ጉዳት

·         በልብዎ ላይ ጉዳት ያደርሳል፦ምናልባትም ለሕይወት አስጊ የሆኑ የልብ ችግሮች ያስከትላል

·         የፅንስ ሞት ወይም የፅንስ መጨንገፍ

·         ለህልፈተ ህይወት ወይም ለሞት መዳረግ


You May Also Like

24 Hour Emergency

Open round the clock for conve-nience, quick and easy access

Complate Lab Services

Cost-efficient, comprehensive and clinical laboratory services

Medical Professionals

Qualified and certified physicians for qulity medical care

EMERGENCY CALL: