SHASHE MEDIUM CLINIC

Call us for any question

0468103905 / 0993788686

Shashemenne Jamaican Sefer, Behind NOC Gas Station

Ethiopia

Office Hour: 08:00am - 05:30pm

info@shasheclinic.com

አንድ ሰዉ የስኳር ህመም አለዉ የሚባለዉ መቼ ነዉ?

14,January 2121

አንድ ሰዉ የስኳር ህመም አለዉ የሚባለዉ መቼ ነዉ?

አንድ ሰዉ የስኳር ህመም አለዉ የሚባለዉ መቼ ነዉ?

አንድ ሰዉ የሚከተሉትን የህመም ምልክቶች ካሉት የስኳር ህመም ምርመራ ማድረግ አለበት፡፡ እነሱም

1.      ሽንት ቶሎ ቶሎ የሚሸና ከሆነ( በተለይ ማታ ማታ)

2.     ዉሃ ቶሎ ቶሎ የሚጠማዉ ከሆነ

3.     የሰዉነት ክብደት ለመቀነስ ሳይሞክር በራሱ ጊዜ እየቀነሰ ከመጣ

4.     ከወትሮ የተለየ የረሃብ ስሜት የሚያስቸግረዉ ከሆነ

5.     እይታ ላይ ብዥታ ካለዉ

6.     የእጅና እግር መደንዘዝ ወይም መጠቅጠቅ ስሜት ካለ

7.     ከፍተኛ ድካም ስሜት ካለዉ

8.     የቆዳ ድርቀት የሚያስቸግረዉ ከሆነ

9.     ቁስል ኖሮት ቶሎ የማይድን ከሆነ

10.   ከተለመደዉ በተለየ በተደጋጋሚ በህመም መጠቃት ካለዉ

አንድ ሰዉ ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች በከፊልም ይሁን በአብዛኛዉ ካሳየ የደም የስኳር ምርመራ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ምርመራዉን አድርጎ የሚከተሉት መስፈርቶች ካሉት ወይም ካሟላ  የስኳር ህመም አለዉ ይባላል፡፡ እነዚህም፡-

1.      ተፁሞ የሚሰራ የስኳር ምርመራ(Fasting blood sugar test)፡- በዚህ ምርመራ መሰረት  አንድ ሰዉ ቢያንስ ለ8 ሰዓታት ከፆመ በኃላ የደም ናሙና ተወስዶ ዉጤቱ ከ126 ሚሊግ/ዴሲሊና ከዚያ በላይ በሁለት ተለያዩ ምርመራዎች ከተረጋገጠ የስኳር ህመም መኖሩን ያሳያል፡፡

2.     ሄሞግሎቢን ኤ ዋን ሲ ምርመራ( Glycated hemoglobin (A1C) test)፡- ይህ መፆም  የማይጠይቀው  የደም ምርመራ ላለፉት ሁለት እና ሶስት ወራት ያለዎትን የደም ስኳር መጠን ያሳያል ፡፡ በዚህ ምርመራ መሰረት የምርመራዉ ዉጤት 6.5 ፐርሰንትና ከዚያ በላይ ከሆነና በሁለት የተለያዩ ምርመራዎች ከተረጋገጠ የስኳር ህመም እንዳሎት ያሳያል፡፡

3.     ሳይፆም የሚሰራ የደም ስኳር ምርመራ ( Random blood sugar test) ፡-  የደም ናሙና በየትኛዉም ጊዜ ሊወሰድ ችላል( ምግብ ቢመገቡም ሊሰራ ይችላል)፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ በየትኛዉም ሰዓት ይመገቡ ፣ የደም የስኳር መጠኑ ከ200ሚልግ/ዴሲሊ ና ከዚ በላይ ከሆነ የስኳር ህመም መኖሩን ያመለክታል፡፡

 

አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ወደ ቦሌ ሚካኤል የሚወስደዉ መንገድ ላይ ርዋንዳ ኤምባሲ አጠገብ እንገኛለን።

ስልክ፡- 0940464646 / 0940565656

You May Also Like

24 Hour Emergency

Open round the clock for conve-nience, quick and easy access

Complate Lab Services

Cost-efficient, comprehensive and clinical laboratory services

Medical Professionals

Qualified and certified physicians for qulity medical care

EMERGENCY CALL: